barber

ስለ እኛ

እንኩዋን ወደ TS Afro የውበት ሳሎን በደህና መጡ. ። ሳሎናችን በኦስሎ ከተማ ፥ በግሩንሎካ Markveien 32 የደንበኞቻችን ምቾት በሚጠብቅ ውብና ዘመናዊ በሆነ መልኩ ተዘጋጅቶ ይጠብቃቹሀል። ከኦስሎ ሴንትሩም ትሪኮችና ባሶች በየ15 ደቂቃ ልዩነት ከሎካላችን የ3 ደቂቃ ርቀት በሚገኝ የትራንስፖርት ማቆሚያ ፌርማታዎች ያደርስዎታል። በግሩንሎካ ዙሪያ የሚገኙ የተለያዩ ሱቆች፥ ካፊቴሪያዎች፥ ሬስቶራንቶችና ፓርኮች ለብዙ ሰዎች የግዜ ማሳለፊያ ተመራጭ ቦታ አድርገውታል። የቀጠሮ ሰአትዎ እስኪደርስ ዘና ብለው የሚጠብቁበት ስፍራ ነው።

የፅጉሮዎትን ውበትና ጤንነት ለመንከባክብ፥ በሙያዊ ትምህርትና በረጅም አመት የስራ ልምድ በምታገዝ አገልግሎት የሚሰጡ ባለሙያዎች አሉን። በተለያዩ ምክንያቶች የተጎዳና የሚሰባበር ፅጉርን የሚጠግን ጥራት ያላቸው የፅጉር ምርቶችን በመጠቀም ፅጉሮዎን እንከባከባለን። የተዘጋጁ ትክክለኛ ወይም አርተፊሻል ፅጉሮችን በስፌት እንዲሁም የተለያዩ ዘዴዎችን በመጠቀም ፅጉርን የማስረዘም ብቃታችን በኦስሎና አካባቢዋ በሚኖሩ ደንብኞቻችን አድናቆትን ያገኘንበትና ተመራጭነት ያተረፍንበት ሞያችን ነው። ባህላዊም ሆነ ዘመናዊ ሽሩባዎች ፥ ራስታ ቁጥርጥሮች፥ ትዊስቶችን ለሴቶችና ለወንዶች በሚስማማ መልኩ እንሰራለን። ኤንደደንበኞቻችን ፍላጎትና ምርጫ ፥ ለተለያዩ ባህላቶችና ዝግጅቶች የሚስማሙ በፅጉር ስታይሎች እናስውቦታለን። የፀጉር ጤንነትንና ውበትን የሚጠብቁ ጥራት ያላቸው ፕሮዳክቶችንና ቅባቶች በተመጣጣኝ ዋጋ እንሸጣለን።

የሳሎናችን ዋነኛ መርህ ከደንበኞቻችን ጋር ጠንካራ የሆነ ቤቴሰባዊ ግንኙነት መፍጠር ነው። ባለሞያዎቻችን ችሎታን ከትህትና ጋር የተላበሱ፥ ለደንበኞች ፍላጎት የሚተጉና ፥ ሁሌም ከደንበኞች የሚቀርብላቸውን አስተያይቶች የሚቀበሉና የሚያከብሩ ናቸው። የTS Afro style ሳሎን ቤተሰብን ይቀላቀሉ፥ ይረኩበታል።

barber
Waiting for more content to be appended ....

እኛን ተከተሉ

2025 Ts afro as | መብቱ በህግ የተጠበቀ ነው። | Powered by: 3ack